የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት እና የዓለምአቀፍ የእንስሳት ምርምር ኢንስቲትዩት በብዝሃ ሕይወት ጥበቃ እና ምርምር ዙሪያ በትብብር ለመስራት ተስማሙ፡፡
የአለም አቀፍ የእንስሳት ምርምር ኢንስቲትዩት በኢትዮጵያ በዋና ዳይሬክተሩ ተወካይ እና ምክትል ዋና ዳይሬክተር የተመራ የልኡካን ቡድን ከአዳዲሶቹ የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት አመራሮቹ ጋር በመገናኘት በኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት የክብር ጉብኝት አድርጓል።
በውይይቱም ሁለቱም ተቋማት የቆየውን አጋርነታቸውን ለማጠናከር ያለመ ውጤታማ ውይይት አድርገዋል። ዋና የትብብር መስኮች የአቅም ግንባታ፣ የጀርም ፕላዝም ልውውጥ እና የጋራ የምርምር እና ልማት ውጥኖች ይገኙበታል።
የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት እና የዓለምአቀፍ የእንስሳት ምርምር ኢንስቲትዩት ትብብሮችን በማሳደግ፣ የጋራ ዕውቀትን በማጎልበት፣ የብዝሀ ሕይወት ጥበቃና ዘላቂ ልማትን በኢትዮጵያ ለማሳደግ ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።
"ከተፈጥሮ ጋር መስማማት ለዘላቂ ልማት" IBD 2025
