በኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የስልጠና፣ ማማከር፣ ፕሮጀክት ክትትልና ድጋፍ ምርምር መሪ ሥራ አስፈጻሚ አስተባባሪነት መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም በኢንስቲትዩት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ሴሚናር ተካሄደ፡፡
ዶ/ር ሳምሶን ሺመልስ የስልጠና፣ ማማከር፣ ፕሮጀክት ክትትልና ድጋፍ ምርምር መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሴሚናሩን ያስጀመሩ ሲሆን Jorge Francisco Soares (Executive Director of Bewild Aid) “The Largest Wildlife Rescue Facility in the World” በተሰኘ ርዕስ ሰነድ አቅርበው በበርካታ ሀገራት ያላቸውን ተሞክሮና በኢትዮጵያ እያከናወኑ ያሉትን ተግባራት ዘርዝረዋል፡፡
በሴሚናሩ ላይ የተሳተፉ የኢንስቲትዩቱ አመራሮችና ተመራማሪዎች የተለያዩ ጥያቄዎችን አቅርበው ምላሾች ተሰጥተዋል፡፡ በቀጣይም ሁለቱም አካላት በጋራና በትብብር ለመስራት ፍላጎታቸውን ገልጸው ሴሚናሩ ተጠናቋል፡፡
