You are currently viewing The Ethiopian Biodiversity Institute launched its first round of the Green Footprint Program

የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት የመጀመሪያዉን ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር አከናወነ

የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል የ2017 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በኩራ ጂዳ ወረዳ አምስት ሺ ችግኞችን ተከለ፡፡

 የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ካርታ ካስኬ መርሀ ግብሩን ባስጀመሪበት ወቅት እንደገለጹት መስሪያ ቤታችን በዘንድሮ አረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር አስር ሺ ሀገር በቀል ችግኞችን የሚተክል ሲሆን ዛሬ አምስት ሺ ሀገር በቀል ችግኞች ይተከላሉ ብለዋል፡፡ በመጥፋት ላይ ያሉ፣ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸዉና ሀገር በቀል ችግኞች መትከል የመስሪያ ቤታችን ዓላማ በመሆኑ ይህን መሰረት ያደረገ መሆኑን አክለዋል፡፡

የደንና ግጦሽ መሬት እፅዋት ምርምር መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ አበራ ስዩም የ2017 የችግኝ መርሀ ግብር “በመትከል ማንሰራራት” ስንል እንተክላለን፣ እንንከባከባለን፣ እናፀድቃለን በዚህም ኢትዮጵያ ታንሰራራለች ብለዉ መሪ ቃሉ መርሀ ግብሩን በሚገባ የሚገልፅ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ደንን መሰረት ያደረገ የብዝሀ ህይወት ሀብት መጠበቅ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለዉምና አተካከሉም ሆነ ችግኞችን ይዘዉ ወደ ተከላዉ ሲሄዱ ጥንቃቄ እንደሚገባ ሞያዊ ምክራቸዉን ለግሰዋል፡፡