You are currently viewing A delegation from the Ethiopian Biodiversity Institute visited the renovation of a home for the disabled in Gelan Guda Sub-district, Sheger City.

የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት ልዑካን በሸገር ከተማ በገላን ጉዳ ክፍለ ከተማ ነሐሴ 22/2017 ያስጀመረውን የአቅመ ደካሞች ቤት እድሳት ጎበኘ።

ወ/ሮ አልማዝ ከበደ የተቋሙ የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ልዑኩን የመሩ ሲሆን ጅምሩና ሥራዉ ጥሩ እየሄደ መሆኑንና የተሻሉ ያሏቸውን ምክረ ሃሳብ ሰጥተው ባለሙያዎቹንና የክፍለ ከተማውንና የወረዳውን የሥራ አስፈፃሚ አካላት ክትትልና ድጋፍ አድንቀዋል።

አቶ ማስረሻ የማነ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈፃሚ ሥራውን በቅርበት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገርና በመከታተል ቤቶቹን በ3 ወር አጠናቆ ለማስረከብ መስከረም 10 /2018 ዓ.ም በሥፍራው ተገኝተው ያለበትን ደረጃ ቃኝተዋል።

በሸገር ከተማ የገላን ጉዳ ክፍለ ከተማ ምክትል ሥራ አስፈፃሚ ፣ በተለይም የዳለቲ ወረዳ ቤቶች ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ኢማን ዑስማን ጉንጃ በተደረገው ሰው ተኮር ሥራ በክፍለ ከተማው፣ በወረዳችውና በአካባቢው ማህበረሰብ ሥም የተሰማቸውን ደስታ በመግለፅ ለኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት መስጋናቸውን አቅርበዋል።

በተጨማሪም የክ/ከተማው ውሃና ኢነርጂ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተገኝተው የወ/ሮ ምህረትን ቤት አፍርሶ በመገንባት ሂደት ላይ የሚፈጠር የሥራ መደናቅፍና መጓተት እንዳይኖርና ነዋሪዋ እናትም እንዳይቸገሩ በውሃ መስመር ጥገና የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገልፀው ለብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት የላቀ ምስጋና አቅርበዋል።