የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት በዋና ዳይሬክተር እና በምክትል ዋና ዳይሬክተር ይመራል፡፡ የማኔጅመንትና የምክክር ኮሚቴው ተጠሪነታቸው ለዋና ዳይሬክተሩ ነው፡፡ የማኔጅመንት ኮሚቴዉ የሁሉም የሥራ ክፍሎችን ሥራ አስፈጻሚዎች ያቀፈ ሲሆን፣ የምክክር ኮሚቴው ደግሞ የማኔጅመንት አባላትን፣ የፕሮጀክት አስተባባሪዎችን እና የቡድን መሪዎችን የያዘ ነው፡፡

ኢንስቲትዩቱ ሰባት መሪ ሥራ አስፈጻሚዎች ያሉት ሲሆን፣ እነርሱም፡-

    • የእንስሳት ብዝሀ ሕይወት ምርምር መሪ ሥራ አስፈጻሚ
    • የአዝዕርትና ሆርቲካልቸር ብዝሀ ሕይወት ምርምር መሪ ሥራ አስፈጻሚ
    • የደንና ግጦሽ መሬት ዕፅዋት ብዝሀ ሕይወት ምርምር መሪ ሥራ አስፈጻሚ
    • የጀነቲክ ሀብት አርክቦትና ጥቅም ተጋሪነት ምርምር መሪ ሥራ አስፈጻሚ
    • የደቂቅ አካላት ብዝሀ ሕይወት ምርምር መሪ ሥራ አስፈጻሚ
    • የስልጠና፣ ማማከርና ፕሮጀክት ክትትልና ድጋፍ መሪ ሥራ አስፈጻሚ
    • የማዕከላትና ዕፅዋት አፀዶች አስተባባሪ

እንዲሁም አስር የአስተዳደር ዘርፍ ሥራ አስፈጻሚዎች ያሉት ሲሆን፣ እነርሱም፡-

        የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ
    • የመሠረታዊ አገልግሎት ሥራ አስፈጻሚ
    • የሰው ሀብት አስተዳደርና ብቃት ሥራ አስፈጻሚ
    • የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሥራ አስፈጻሚ
    • የተቋማዊ ለውጥ ሥራ አስፈጻሚ
    • የግዥና ፋይናንስ ሥራ አስፈጻሚ
    • የስትራቴጅክ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ

        የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ

    • የኦዲት ሥራ አስፈጻሚ
    • የሥነ- ምግባርና የፀረ-ሙስና ሥራ አስፈጻሚ
    • የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ
    • የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ

 በተጨማሪም ሰባት ማዕከላት፣ ሁለት እፅዋት አጸዶች እና አንድ ጂን ባንክ ያሉት ሲሆን፣ እነርሱም፡-

  •   ማዕከላት
    • አሶሳ ብዝሀ ሕይወት ማዕከል
    • ባህር ዳር ብዝሀ ሕይወት ማዕከል
    • ጎባ ብዝሀ ሕይወት ማዕከል
    • ሀረር ብዝሀ ሕይወት ማዕከል
    • ሀዋሳ ብዝሀ ሕይወት ማዕከል
    • መቀሌ ብዝሀ ሕይወት ማዕከል ዳይሬክተር
    • መቱ ብዝሀ ሕይወት ማዕከል ዳይሬክተር
  •   እፅዋት አጸዶች
    • ጅማ እፅዋት ማዕከል
    • ሻሸመኔ የዕፅዋት አፀድ
  •   ጂን ባንክ
    • ፍቼ ጂን ባንክ