የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት አመራሮችና የማኔጅመንት አባላት በቢሾፍቱ ከተማ ጨለለቃ ክ/ከተማ ሆራ አርሰዲ ልዩ ስሙ ሆራ ሀይቅ በመገኘት ሀገር በቀል ችግኞችን የመትከል መርሀ ግብር አከናውነዋል ።
በተከላዉም የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ፣ የቢሾፍቱ ከተማ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ፣ አባገዳዎች ፣ DSW የጀርመን ፋዉንዴሽን ፣ የአካባቢው የሴፍትኔት አባላትና ህብረተሰቡ ተሳትፈዋል ።
በልዩ የአባ ገዳዎች ምርቃትም መርሀ ግብሩ ተከፍቷል ።
የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ካርታ ካስኬ በቦታው በመገኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዉ ፤ ኢንስቲትዩቱ የደን ስርዓተ_ምህዳር በተሻለ መልኩ ተጠብቆ እንዲቆይ የማድረግ ስራን ያከናውናል ብለዋል።
አክለውም በሀገራችን ያሉ ሀገር በቀል ዝርያዎች፣ እየጠፋ ያሉትን ፣ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸውና በርካታ አገልግሎት የሚሰጡ ሀገር በቀል ዝርያዎችን የመጠበቅ ስራ እንደሚሰራ ተናግረዋል ። አረንጓዴ አሻራ ለኛ እንደ እድል ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ 21ሚሊየን ሀገር በቀል ችግኞችን ለአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ኢንስቲትዩቱ አበርክቷል ብለዋል ።
የኢንስቲትዩቱ ማዕከላትም በሚገኙበት አካባቢ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብርን ከባለድርሻ አካለት ጋር በመሆን እያከናወኑ መሆናቸውን ገልፀዋል ።
ተቋማችን አረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የሰጠንን ዕድል በበጎነትና በትጋት እየተሳተፈ ነው በማለት ችግኙን ስንተክል በጥንቃቄ እንዲፀድቅ አድርገን መሆን አለበት በማለት የተሳተፉትን አካላት አመስግነዋል ።
