ተግባርና ኃላፊነት
- የጀነቲክ ሀብትና ተያያዥ የማህበረሰብ እውቀት ላይ አርክቦት ፈቃድ መስጠት (ለምርምር፡- ከአገር ውስጥ የማስወጫ፣ ወደ አገር ውስጥ ማስገቢያ፣ የአሰሳና ልዩ ፈቃድ መስጠት እና ለንግድ ዓላማ የአርክቦት ፈቃድ የመስጠት) ሥራን ማከናወን፣
- ህገ-ወጥ የጀነቲክ ሀብት ዝውውር፣ ቁጥጥርና ክትትል ማድረግ፣
- የብዝሀ ሕይወት ሀብት ደህንነት እንዲጠበቅ፣ ህጋዊ የጀነቲክ ሀብት አርክቦትና ፍትሃዊ ጥቅም ተጋሪነት እንዲሰፍን ማድረግ፣
- ከብዝሀ ሕይወት ጋር ተያያዥ የሆኑ የማህበረሰብ እውቀት፣ ፈጠራና ልምዶች አሰሳና ምዝገባ ጥናት ማከናወን፣
- የግንዛቤ ማዳበሪያ ፅሑፎች (በራሪ ፅሑፎች፣ ብሮሹሮች፣ ዜና መፅሔቶች፣ መፅሔቶች፣ ቡክሌቶች፣ ጋዜጣ) እና የምርምር ውጤቶችን ማሳተምና ማሰረጨት ፣
- በአርክቦትና ጥቅም ተጋሪነት ሥርዓት አፈፃፀም ፣ የባለድርሻ አካላትን ግንዛቤ ማሳደግ፣
- በልውጠ ሕያዋን እና ወራሪ መጤ ዝርያዎች ዙሪያ ክትትል፣ ቁጥጥር እና አሉታዊ ተጽዕኖ ግምገማ ማድረግ
- የወራሪ መጤ ዝርያዎች ፖሊሲዎችን፣ ስትራቴጂዎችንና የድርጊት መርሀ-ግብሮችን መተግበር
- ለጥቅም ተጋሪነት የሚውሉ ዝርያዎች ፍላጎትን የመለየትና በተለዩት ላይ የዋጋማነት ትመና እና የባዮፕሮስፔክቲንግ የምርምር ጥናት ማካሄድ፣
- ከጀነቲክ ሀብትና ተያያዥ የማህበረሰብ እውቀት አርክቦት ፈቃድ የተገኙ ጥቅሞች ፍትሃዊና ሚዛናዊ እንዲሆኑ የሚያስችሉ የሕግ ማዕቀፎች እንዲዘጋጁና እንዲሻሻሉ ማድረግ
በመሪ ሥራ አስፈጻሚ ክፍሉ በኩል የምንሰጣቸው አገልግሎቶች
- ለምርምር (ለንግድ ላልሆነና) ዓላማ የጀነቲክ ሀብትና ተያያዥ የማህበረሰብ እውቀት የአርክቦት ፈቃድ መስጠት፣
- ለጥቅም ተጋሪነት (ለንግድ) ዓላማ የጀነቲክ ሀብትና ተያያዥ የማህበረሰብ እውቀት የአርክቦት ፈቃድ መስጠት እና
የተመረጡ ህትመቶች
- Opportunities for Bioprospecting Genetic Resources in Ethiopia (Published).
- Economic Valuation of Moringa stenoptala in Wolayita, Konso, Arba Minch and Jinka (Past).
- Economic Valuation of Thymus (Thymus schimperi and Thymus serrulatus) in North Shewa Zone, Ethiopia (Past).
- Ethno-botanical study of Enset (Ensete ventricosum) in Angacha Woreda (Past).
- Bioprospecting potential of Ocimum americanum and Ocimum basilicum for access and benefit sharing around selected areas of North Gondar and West Gojjam, Ethiopia (Ongoing).
- Economic Valuation of Rhizobium (Rhizobial bio-fertilizers) in Northern Shewa, Wolayita and Arsi Zones: Baseline study for access and benefit sharing (Ongoing).
- Traditional knowledge study related to herbal medicinal plants around selected zones of Southern Nations Nationalities, and Peoples Regional States (Ongoing).
- Assessment of Mimosa diplotricha (Mimosa invisa) around selected woredas of Jimma Zone (Ongoing).