ኢንስቲትዩቱ የብዝሀ ህይወት ሀብቶችን ጥቅም የማካፈል ተልዕኮን ለማሳካት እየሰራ ነው
ቀረጥ በተባለ ተክል (Osyris quadripartita) ስምምነት ላይ በተመለከተ የምክክር መድረክ ከኤፕሪል 27-28 ቀን 2018 ተካሄደ።
የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ፈለቀ ወልደየስ እንዳሉት ተቋሙ የዓለም አቀፍ ብዝሀ ሕይወት ጥበቃ ስምምነቱን ሦስቱ መሠረታዊ ዓምዶች ለማሳካት እየሠራ ነው። በዚህ መሠረት ኢንስቲትዩቱ በሀገሪቱ ያሉትን የብዝሀ ህይወት ሀብቶችን ጥቅም የማካፈል ተልዕኮን ለመፈጸም እየሠራ ነው።
ዶ/ር ፈለቀ እንደተናገሩት ከብዝሀ ሕይወት ሀብቶች ጋር አብረው የኖሩ ፣ በብዝሀ ሕይወት ሀብቶች ላይ ተጽዕኖ የሚይሳድሩ እና ብዝሀ ሕይወት ለውጥ ላይ ቀጥተኛ ግኑኝነት ያላቸው ማህበረሰቦች ለጥቅም መጋራት መሠረት እንደሆኑ ተናግረዋል።
የሀገሪቱን የብዝሀ ሕይወት ሀብት ወደ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሸጋገርና ያለውን ጥቅም ለማካፈል የሚያስችል ሥርዓት መፈጠሩን ጠቁመዋል። ስለዚህ የጄኔቲክ ሀብት ሽግግር ከህጋዊ መስፈርቶች ጋር የተቆራኘ ነው ብለዋል።
የጄኔቲክ ሀብትና ጥቅም ተጋሪነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አሸናፊ አየነው በበኩላቸው ፍትሃዊ እና ሚዛናዊ ጥቅማ ጥቅሞችን ለማረጋገጥ አዋጅና ደንቦች አሉ ብለዋል።
በዚህ መሠረት የዶኮሞ ኦይልስ ፒኤልሲ መዋቢያዎችን ከቀረጥ (Osyris quadripartita) ለማምረት ፈቃድ ተሰጥቶታል።
ይህ ደግሞ ተክሉ በዘላቂነት ጥቅም ላይ እንዲውል ያግዛል ብለዋል አቶ አሸናፊ፥ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች ያለማቋረጥ እንደሚሰጡም ተናግረዋል።
ተሳታፊዎች የቴክኒክ ሥልጠና በመሰብሰብ ሂደት መከናወን እንዳለበትና የባለድርሻ አካላት ሚና ታሳቢ መሆን እንዳለበት አስተያየት ሰጥተዋል።
የዶኮሞ ኦይልስ ፒኤልሲ ጋር የተደረገው ስምምነት ለ 10 ዓመታት ይሠራል።
የምክክር መድረኩ በ Global ABS ፕሮጀክት በገንዘብ ተደግፏል።