You are currently viewing Monthly Scientific Seminar Presented

ወርሀዊ ሳይንሳዊ ሴሚናር ቀረበ

በኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የምርምር፣ ሥርፀትና ፕሮጀክት አመራር ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት ወርሀዊ ሳይንሳዊ ሴሚናር ጥቅምት 02 ቀን 2014 ዓ.ም ቀረበ፡፡

ሴሚናሩን በንግግር የከፈቱት በኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የምርምር፣ ሥርፀትና ፕሮጀክት አመራር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ተስፋዬ አዋስ ሲሆኑ በቀጣይ ሴሚናሩ በየወሩ እንደሚቀርብ ተናግረዋል፡፡

በሴሚናሩ ላይ ዶ/ር ዮሴፍ ገብረሀዋርያት "ባዮቨርሲቲ ኢንተርናሽናል፣ ኢትዮጵያ፣ካንትሪ ሪፕረዘንታቲቭ " "From a Gene to a Table" በተሰኘ ርዕስ ላይ ጽሁፍ አቅርበው ውይይት ተካሂዶበታል፡፡ ዶ/ር መለሰ ማሪዮ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ውይይቱን የመሩ ሲሆን ከተሳታፊዎች ለቀረቡ ጥያቄዎች በጽሁፍ አቅራቢውና በሚመለከታቸው አካላት ምላሾች እንደተሰጠባቸው የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዘግቧል፡፡