የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ማመዴ ቀበሌ በቀዳማዊት ክብርት ዶ/ር ዝናሽ ታያቸው ጽ/ቤት በተገነባው የረገ ኤያት 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ሰኞ ሀምሌ 17 ቀን 2015 ዓ.ም የሀገር በቀል ችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር አከናወነ፡፡
በመርሀ-ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች፣ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተወካዮች፣ የጉራጌ ዞን አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ሰራተኞች፣ የአበሽጌ ወረዳ አመራሮች፣ የክረምት በጎ አድራጎት ፍቃደኞችና የአካባቢው ነዋሪዎች በተገኙበት ተከናውኗል፡፡
መርሀ-ግብሩን በተመለከተ የተለያዩ መልዕክቶች በዶ/ር መለሰ ማርዮ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር፣ ዶ/ር ፈለቀ ወልደየስ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር፣ ዶ/ር ዮሀንስ ገብሩ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዘዳንት፣ አቶ ምህረት ወንባርጋ የጉራጌ ዞን አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ እንዲሁም አቶ ዘመተ አይፎክሩ የአበሽጌ ወረዳ ም/አስተዳዳሪ እና የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ ተላልፈዋል፡፡
በት/ቤቱ ቅጥር ግቢ ጉብኝት የተካሂደ ሲሆን በሀገር ሽማግሌዎች ምርቃት መርሀ-ግብሩ ተጠናቋል፡፡