በኢትዮጵያ ብዝኃ ህይወት ኢንስቲቲዩት አቶ ማስረሻ የማነ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈፃሚ የዓለም አቀፉ የኢኮኖሚ አዝማሚያ በኢትዮጵያ ላይ ያለው አንድምታ እና የተቋሙ የ9 ወር የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ለሰራተኞች አቅርበዋል።
የሃገራችን ኢኮኖሚያዊ የመንግሥት ተቋማት ሪፎርም እና ዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮችን ከለውጥ፣ ውጤትና እድገት አንፃር ከተቋማት ዕቅድና አፈፃፀም ጋር አስተሳስረው የመንግሥት ሠራተኛውን ድርሻ አመላክተዋል። በተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚና ምርታማነት ተወዳዳሪ የመሆናችን ሚስጢርም በተለይ በግብርናው ዘርፍ የተገኙ ውጤቶች መሆናቸውን የሁለት ተከታታይ ዓመታት የገቢና የወጪ ንግድ ውጤት በንፅፅር ለሰራተኛው በሰነዳቸው አሳይተው አጠቃለዋል።
የግብርና ሚኒስትር የተፈጥሮ ሃብት አማካሪ አቶ ታረቀኝ ፅጌ ፤ ከዶክተር ካርታ ካስኬ የኢትዮጵያ ብዝኃ ህይወት ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር እና ከዶክተር አብዮት ብርሃኑ የኢትዮጵያ ብዝኃ ህይወት ኢንስቲቲዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ጋር በመሆን ውይይቱን መርተዋል። በሰነዱ የተመለከቱ ጭብጦች፣ ገንቢ ሀሳቦችና ጥያቄዎች ከሰራተኞች የቀረቡ ሲሆን በተለይም እንደ ብዝኃ ህይወት ምርምርና ጥናት፤ ዘሮችን መሰብሰብና ማንበር ፤ አግልግሎትና ተጠቃሚነት ላይ ያተኮሩ ተግዳሮቶች ተነስተው አወያዮችም በየድርሻቸው ተስፋ ሰጪ ምላሾች ሰጥተውባቸዋል።
በመጨረሻም ዶ/ር ካርታ ካስኬ የኢትዮጵያ ብዝኃ ህይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር እንደተቋም የሚከናወኑ ተግባራት በሃገር ኢኮኖሚ ግንባታ ላይ ሰፊ ለውጥ ለማምጣት ሠርተኞች በሙያችን በትጋት ያለመታከት እየሰራን ተግዳሮቶችን እየፈታን መሄድ ይገባናል፤ ካሉ በኋላ ሁላችንም ወደ ራሳችን ልንመለከት ይገባል፤ እያንዳንዱ ሰራተኛ ለሀገራዊ ዕድገትና ብልፅግና የበኩሉን አስተዋጽኦ ሊወጣ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል፡፡
