You are currently viewing The signing ceremony of the Quadripartite Memorandum of Understanding took place

የአራትዮሽ የመግባቢያ ሰነድ የፊርማ ሥነሥርዓት ተከናወነ

የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በመድሀኒታማ ዕጽዋት ማንበርና ምርምር ማካሄድ የሚያስችል የአራትዮሽ የመግባቢያ ሰነድ የፊርማ ሥነሥርዓት የካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም አከናወነ፡፡

ስምምነቱን የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት፣ የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ፣ የአርማወር ሃንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት እና የወንዶ ገነት የግብርና ምርምር ማዕከል በአርማወር ሃንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት የመሰብሰቢያ አዳራሽ አከናውነዋል፡፡

የስምምነት ፊርማቸውን ዶ/ር መለሰ ማርዮ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር፣ ፕሮፌሰር ንጉሴ ደቻሳ የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር፣ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ የአርማወር ሃንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር እና ዶ/ር ሳራ ሽኩር የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ፤ ምርምር ፤ቴክኖሎጅ ሽግግር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት አስፍረዋል፡፡

አራቱም አካላት በመድሀኒታማ ዕጽዋት ማንበርና ምርምር ዘርፍ ያላቸውን ተሞክሮ በማካፈልና በቀጣይ ጥናት የበኩላቸውን ለመወጣት ቁርጠኝነታቸውን አሳይተዋል፡፡