ለኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የማኔጅመንት አባላት የማነቃቂያ ስልጠና ግንቦት 02 ቀን 2017 ዓ.ም ተሰጠ፡፡
ስልጠናውን ዶ/ር አብዮት ብርሃኑ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር ባስጀመሩበት ወቅት የተለወጠ አመራር ለውጥ እንደሚያመጣ አስታውሰው አመራርነት ከቴክኖሎጂ ጋር መቆራኘት እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡
ስልጠናው በአቶ ዘመኑ ጋሻው በኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት የስልጠና ዳይሬክተር እና ከፍተኛ አማካሪ ሳቢና ማራኪ በሆነ መልኩ የተሰጠ ሲሆን ከማኔጅመንት አባላትም የተለያዩ አስተያየቶች ተሰጥተዋል፡፡
በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ ወ/ሮ አልማዝ ከበደ በኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈጻሚ ለኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
