ዓለም አቀፍ የብዝሀ ሕይወት ቀን በዓል Building a shared future for all life “ለሁሉም የጋራ የወደፊት ህይወት መገንባት” በሚል መሪ ቃል ግንቦት 12 ቀን 2014 ዓ.ም በInter Lexury Hotel ተከበረ፡፡
በበዓሉ መክፈቻ ላይ ዶ/ር ገመዶ ዳሌ ብዝሀ ሕይወትን ለመጠበቅ መረጃዎችን በማመንጨት ለሚመለከተው አካል የማቅረብና መወሰድ የሚገባቸውን እርምጃዎች ማሳየት ይጠበቃል ብለዋል፡፡
በዓሉን የተመለከተ ሰነድ ዶ/ር መለሰ ማሪዮ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ያቀረቡ ሲሆን የብዝሀ ሕይወት ጥፋትን ለማስቆም የተቀረጹ እርምጃዎችን በዝርዝር አቅርበዋል፡፡ በዓሉ የሚከበርባቸው ምክንያቶች ግንዛቤ ለመፍጠር፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን ለማስተዋወቅ እና ለብዝሀ ሕይወት ድጋፍ ለማግኘት መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
አቶ አብደታ ሮቢ BIODEV2030 National Diagnostic Result ዙሪያ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በቀረቡ ሰነዶች ላይ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡