የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ብዝሀ ሕይወትን በመጠበቅና ዘላቂ ጥቅም እንዲሰጡ ለማድረግ የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ከሀገሬ ኸርባል ጋር ተፈራረመ፡፡
የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መለሰ ማሪዮ እንደገለፁት ህይወታዊ ሀብቶችን በመጠበቅ ዘላቂ ጥቅም እንዲሰጡ ማድረግ ዋናዉ የኢንስቲትዩቱ ተልዕኮ መሆኑን ገልፀዉ 10 በሚሆኑ ህይወታዊ ሀብቶች በመጠቀም ሊሰራ ከፈለገዉ ሀገሬ ኸርባል ጋር ይህንን ስምምነት መፈራረማቸዉን ገልፀዋል፡፡
አክለዉም ዋና ዳይሬክተሩ ከዚህ ቀደም በርካታ ህይወታዊ ሀብቶች ላይ ኢንስቲትዩቱ በጋራ ለመስራት የጋራ መግባቢያ ሰነድ መፈራረሙን ገልፀዉ የዛሬዉም የዛ አካል መሆኑና የተጀመረዉ ስራ እንዲሰፋና ዉጤታማ እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡
የሀገሬ ኸርባል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰብስቤ በላይ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት በጋራ አብሮ ለመስራት ፍቃደኛ በመሆኑ አመስግነዉ 10 በሆኑ ሀገር በቀል አዝርዕቶችን ላይ የኸርባል ምርቶችን ለማምረት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡