You are currently viewing Discussion Held with Members of the Chinese Academy of Sciences Delegation

ከቻይና የሳይንስ አካዳሚ ልዑካን ቡድን አባላት ጋር ውይይት ተደረገ

የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ከቻይና የሳይንስ አካዳሚ ልዑካን ቡድን አባላት ጋር ማክሰኞ ጥር 14 ቀን 2016 ዓ.ም በኢንስቲትዩቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት አደረገ፡፡ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መለሰ ማርዮ ለልዑካን ቡድኑ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈው ስለ ኢንስቲትዩቱ አጠቃላይ መረጃዎችና የሚያከናውናቸውን ተግባራት በዝርዝር አቅርበዋል፡፡

ፕሮፌሰር Yunting Fang የ Institute of Applied Ecology (IAE) ም/ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸው ስለ ኢንስቲትዩታቸው ገለጻ አቅርበው ውይይት ተደርጓል፡፡ በውይይቱ ወቅት ዶ/ር ፈለቀ ወልደየስ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር ቻይና እና ኢትዮጵያ የሚያመሳስላቸው በርካታ ጉዳዮች መኖራቸውን አስታውሰው በትብብር የምንሰራቸው በርካታ ርዕሰ-ጉዳዮች አሉ ብለዋል፡፡

በሁለቱም ተቋማት መካከል በጋራ መስራት የሚቻልባቸውን ጉዳዮች በመለየት የመግባቢያ ሰነድ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ ለመግባት ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡