በኢፌዴሪ የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ግርማ አመንቴ እና የልዑክ ቡድናቸው ዓርብ የካቲት 22 ቀን 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ውይይት አደረጉ፡፡ ውይይቱን ከኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ መሪ ሥራ አስፈጻሚዎች፣ ሥራ አስፈጻሚዎችና የቡድን መሪዎች ጋር አድርገዋል፡፡
ዶ/ር መለሰ ማርዮ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ስለ ተቋሙ አጭር ሰነድ አቅርበዋል፡፡ ዶክተር ግርማ አመንቴ በኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ብሔራዊ ባንክ ከሚጠብቀው ወርቅ በላይ ሀብት መኖሩን አስታውሰው ውይይት ማድረጉ ለቀጣይ ስራዎች ወሳኝነት እንዳለው ተናግረዋል፡፡ አይዘውም ከመቼውም ጊዜ በላይ ለተፈጥሮ ሀብትና አካባቢ ጥበቃ ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠበት ወቅት በመሆኑ ሀብቱን ማስተዋወቅና ጥቅም ላይ በማዋል ለሀገራዊ ዕድገት ያበረከተውን አስተዋጽኦ መግለጽ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
ዶ/ር ፈለቀ ወልደየስ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸው በውይይቱ ደስተኛነታቸውን ገልጸው የጀማመርናቸውን ተግባራት በማስፋት ውጤታማ ሥራ እንሰራለን ብለዋል፡፡ ከተወያዮችም የተለያዩ ሀሳቦችና ጥያቄዎች የቀረቡ ሲሆን ምላሾችም ተሰጥተዋል፡፡ በመጨረሻም በሚኒስትሩ አቅጣጫዎች የተሰጡ ሲሆን ተወያዮችም ተቀብለው ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኝነታቸውን አሳይተዋል፡፡
