ሀምሌ 14 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ፤ የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት ከፍተኛ አመራሮች ከፈረንሳይ አምባሳደር በኢትዮጵያ አሌክሲ ላሜክና ቡድናቸዉን በዋና ዳይሬክተር ቢሮ ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ያሏትን የብዝሀ ሕይወት ሀብቶች መጠበቅ ወይም ማንበር ፣ በተገቢዉ መንገድ በዘላቂነት መጠቀም እና የጀነቲክ ሀብት አርክቦትና ጥቅም ተጋሪነትን በሚመለከት ተወያይተዋል፡፡ በጋራ የትብብር መስኮች በተለይ ለአየር ንብረት ለዉጥ የማይበገሩ ዘሮችና ተያያዥ ቴክኖሎጂዎች ከጂን ባንካችን ለማህብረሰቡ በሚቀርቡበት ሁኔታ፣ የላብራቶሪ መሰረተ ልማት እና የመስክ መሣሪያዎችን አቅም ግንባታ እንዲሁም በጂን ባንካችን ዉስጥ የተነበሩ ዘሮችን በዝርዝር ጄኖታይፒንግ መርምሮ ማዘጋጀትን በሚመለከት ጥልቅ ውይይት የተደረገ ሲሆን፤ ወደፊት በተመሳሳይ ጉዳዮች ላይ ተቀራርቦ ለመስራት ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
