የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት በዋና ዳይሬክተርና በምክትል ዋና ዳይሬክተር መሪነት በስምንት የምርምር የስራ ሂደቶች፣ በዘጠኝ የአስተዳደር ዘርፍ የስራ ሂደቶች፣ በሰባት የብዝሀ ሕይወት ማዕከላት፣ በሁለት እፅዋት አጸድ ማዕከላት እና በአንድ ዘረ-መል ባንክ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ስምንት የምርምር የስራ ሂደቶች ያሉት ሲሆን እነሱም፡-

  • አዝርዕትና ሆርቲካልቸር ብዝሀ ሕይወት ዳይሬክቶሬት
  • እንስሳት ብዝሀ ሕይወት ዳይሬክቶሬት
  • ደቂቅ አካላት ብዝሀ ሕይወት ዳይሬክቶሬት
  • ደንና ግጦሽ መሬት እፅዋት ብዝሀ ሕይወት ዳይሬክቶሬት
  • የጀነቲክ ሀብት አርክቦትና ጥቅም ተጋሪነት ዳይሬክቶሬት
  • የስርዓተ ምህዳር ዳይሬክቶሬት
  • የቅርንጫፍ ማዕከላትና ባለድርሻ ሴክተሮች ዳይሬክቶሬት
  • የምርምር፣ ስርጸትና ፕሮጀክት ትግበራ ዳይሬክቶሬት

እንዲሁም ዘጠኝ የአስተዳደር ዘርፍ የስራ ሂደቶች እነሱም፡-

  • ሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
  • የግዢ፣ ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
  • የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት
  • የእቅድ፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት
  • የሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
  • ኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት
  • ለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
  • የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
  • የስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት