አዲስ አበባ 14/2017 የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የክልሉን ብዝሃ ሕይወት ፕሮቶኮልና ተያያዥ ስትራቴጂዎች በስራ ላይ አዋለ
የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሚኒስትሮች ስብሰባ ዛሬ ሲጠናቀቅ የኢጋድ ሥራ አስፈፃሚ ጸሐፊ አምባሳደር ማህቡብ ማሊም ፕሮቶኮሉ ሀብትን ለማሰባሰብ እና በክልሉ የስነምህዳር ልማት ጉዳይ ላይ የበለጠ ትብብር ለመፍጠር እንደሚረዳ ተናግረው የአካባቢ ሚኒስትሮች የብዝሃ ሕይወት አስተዳደር ፕሮቶኮልን ማጽደቃቸው “ትልቅ ስኬት ነው” ብለዋል የኢጋድ ሥራ አስፈፃሚ ። እንደ አምባሳደር ማሊም ገለፃ በአፍሪካ ቀንድ ያለው የአካባቢያዊ ኢኮኖሚያዊ ውህደት እውን ሊሆን የሚችለው የተፈጥሮ ሀብቶችን እና ድንበር ተሻጋሪ ሥነ ምህዳሮችን በጥንቃቄ በማስተዳደር ነው።
በቅርቡ ኢትዮጵያ እና ኬንያ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የድንበር ተሻጋሪ ፕሮግራም የጀመሩ ሲሆን በአባል አገራት መካከል በድንበር ተሻጋሪ ትብብር ውስጥ የተገናኙትን ሁሉ ለመርዳት ዝግጁ ነን ብለዋል።
የአካባቢ ፣ ደን እና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስትሩ ዶክተር ገመዶ ዳሌ በበኩላቸው የኢጋድ ክልል በከባድ ድርቅ እና ተደጋጋሚ ረሃብ የሚታወቅ ሲሆን ይህም ከፍተኛ የመሬትን በአግባቡ አለመጠቀም እና የውሃ እጥረት መኖሩን ያንፀባርቃል ብለዋል።
ይህም በሥነ -ምህዳር ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንደሚያሳድርና በክልሉ ውስጥ ለሚኖሩ ህዝቦች ቀጣይነት ያለው ኑሮ ትልቅ ሥጋት መሆኑን ጠቁመዋል።
አያይዘውም በቀጣናው የሚገኙ የብዝሀ ሕይወት ሀብቶችን ለመጠበቅ የዚህ ዓይነት ቀጣናዊ ፕሮቶኮልን መፈራረም ብቻ በቂ አለመሆኑን ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።
በቀጣናው ውስጥ የብዝሀ ሕይወት ሀብቶች በዘላቂነት ለመጠቀም ፕሮቶኮሉን በአግባቡ ለመተግበር የኛ የቁርጠኝነት ወሳኝ ነው ”ብለዋል ዶክተር ገመዶ ዳሌ።