You are currently viewing The 20th International Biodiversity Day was celebrated

20 ኛው ዓለም አቀፍ የብዝሀ ሕይወት ቀን ተከበረ

20 ኛው ዓለም አቀፍ የብዝሀ ሕይወት ቀን “እኛ ለተፈጥሮ የመፍትሔ አካል ነን” በሚል መሪ ቃል ግንቦት 14 ቀን 2013 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብዝሃ ሕይወት ኢንስቲትዩት ቅጥር ግቢ ውስጥ ተከበረ።

የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት አመራሮችና ሠራተኞች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና መገናኛ ብዙኃን በተገኙበት የፓናል ውይይትና የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ተከናውኗል።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መለሰ ማሪዮ “በብዝሀ ሕይወት ውስጥ ብዙ ሰው ሰራሽና ተፈጥሮአዊ ችግሮች አሉ፣ እነዚህን ጉዳዮች በዘላቂነት ለመፍታት መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ከማኅበረሰቡ ጋር በአጋርነት የመሥራት ትልቅ አገራዊ ኃላፊነት አለባቸው ”ያሉ ሲሆን በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለተፈጥሮ የመፍትሔ አካል በመሆኑ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ውስጥ እንድንገባ ያስችለናል ብለዋል።

የፓናል ውይይቱ በተቋሙ ተመራማሪዎች ቀርቦ ለበዓሉ የተመረጠውን ጭብጥ በማብራራት ፣ እየተሠራ ያለውን ሥራ በማስታወስ የወደፊቱን አቅጣጫ በመጠቆም ቀርቧል።

በተባበሩት መንግስታት የብዝሃ ሕይወት ስምምነት መሠረት ዓለም አቀፍ የብዝሃ ሕይወት ቀን በየዓመቱ ግንቦት 14 ቀን ይከበራል። አገሮች በጄኔቲክ ሀብታቸው ላይ ሉዓላዊነት እንዲኖራቸው የብዝኃ ሕይወት ቀን ዋስትና እንደሚሰጥ በመድረኩ ላይ ተገልጿል። ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ የብዝሀ ሕይወት ኮንፈረንስ (ሲቢዲ) 54 ኛ ፈራሚ ሀገር ስትሆን በ 1994 ዓ.ም የብዝሃ ሕይወት ቀንን በማክበር ኢትዮጵያ ከዓለም ቀዳሚና አንዷ ናት።