በኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት የህጻናት ቀን እና የነጭ ሪቫን ቀን በዓል ህዳር 29 ቀን 2015 ዓ.ም በውይይት ተከበረ፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ ህጎች፣ የህጻናት መብት በሀገር ውስጥ ህጎች፣ የዓለም ህጻናት ቀን መቼ መከበር ተጀመረ? አማራጭ የህጻናት ድጋፍና እንክብካቤ፣ ህጻናትን ለአስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ የሚዳርጓቸው ዋና ዋና ምክንያቶችን ያካተተ ሰነድ ወ/ሮ አልማዝ ከበደ በኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ለውይይት አቅርበዋል፡፡
በተጨማሪም የነጭ ሪቫን ቀን በዓል “ሰላም ይስፈን፣ በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚደርስ ጥቃት ይቁም!” በሚል መሪ ቃል በዓሉ እንደሚከበር አስታውሰዋል፡፡
ውይይቱን አቶ መኳንንት እያዩ የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ የመሩ ሲሆን ሰራተኞችም የተለያዩ ሀሳቦችን አቅርበው ለተግባራዊነቱ ድጋፋቸውን እንደሚያደርጉ አረጋግጠው የእለቱ ውይይት መጠናቀቁን የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዘግቧል፡፡