የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት በሚዲያ ዘርፍ በጋራ መስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ከማውንቴንስ ሚዲያ ጋር ሀምሌ 20 ቀን 2015 ዓ.ም በኢንስቲትዩቱ አዳራሽ ተፈራረመ፡፡
በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ ዶ/ር መለሰ ማርዮ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር የብዝሀ ሕይወት መጥፋት መንስዔዎችን ጠቅሰው የተጎዱ ሥነ-ምህዳሮች እንዲያገግሙ በጋራ እንሰራለን ብለዋል፡፡
አቶ አስቻለው ጌታቸው የማውንቴንስ ሚዲያ ስራ አስኪያጅ በበኩላቸው ኅብረተሰቡ የተፈጥሮን ድምጽ መስማት ስላለበት ለብዝሀ ሕይወት ሀብት የሚቆረቆር ኅብረተሰብ ለመፍጠር በጋራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
ፕሮፖዛሎችን በጋራ በመቅረጽና ሀብት በማፈላለግ የብዝሀ ሕይወት ሀብቶችን በሚዲያ የማስተዋወቅ ስራዎች በጋራ እንደሚሰሩ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡